Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 11:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በንጉሡ ላይ ያመፀበትም ምክንያት እንዲህ ነው፤ ሰሎሞን ድጋፍ የሚሆኑ እርከኖች በመሥራት የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥር ይጠግን ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ኢዮርብዓም ለዐመፅ የተነሣሣበትም ታሪክ እንደሚከተለው ነው፥ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጽሮች እየጠገነ በማደስ ላይ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኢዮርብዓም ለዐመፅ የተነሣሣበትም ታሪክ እንደሚከተለው ነው፥ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጽሮች እየጠገነ በማደስ ላይ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እር​ሱም ያደ​ረ​ገው ይህ ነው በን​ጉሡ በሰ​ሎ​ሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዳ​ርቻ ያለ ቅጥ​ር​ንና የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በንጉሡም ያመፀበት ምክንያት ይህ ነው፤ ሰሎሞን ሚሎን ሠራ፤ የአባቱንም የዳዊትን ከተማ ሰባራውን ጠገነ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 11:27
12 交叉引用  

ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፣ የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቷል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፣ “የሰውየው ራስ ተቈርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው።


ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን ዐምባ ያዘ፤ ይህችም የዳዊት ከተማ የተባለችው ናት።


ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።


የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ።


ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።


ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረቦች፣ የአሞንና የአሽዶድ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌም ቅጥር ሥራ እየተፋጠነና ክፍት ቦታዎቹም ሁሉ እየተሞሉ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤ ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።


“ተላላ ሆነህ ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግህ፣ ወይም ክፉ ነገር ካቀድህ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።


የዳዊት ከተማ ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤ በታችኛውም ኵሬ፣ ውሃ አጠራቀማችሁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።


በእግዚአብሔር ቀን በሚሆነው ጦርነት ጸንቶ መቆም እንዲችል፣ የተሰነጠቀውን ቅጥር ለእስራኤል ቤት ለመጠገን ወደዚያ አልወጣችሁም።


“በዚያ ቀን፣ “የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤ የተሰበረውን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹን ዐድሳለሁ፤ ቀድሞ እንደ ነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤


跟着我们:

广告


广告