Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 11:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከፋራንም ሰዎች ይዘው ወደ ግብጽ በመምጣት፣ ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገቡ። ንጉሡም ለሃዳድ ቤትና መሬት ሰጠው፤ ቀለብም አዘዘለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጉዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጒዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከም​ድ​ያ​ምም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከፋ​ራን ሰዎ​ችን ወሰዱ፤ ወደ ግብ​ፅም መጡ፤ ወደ ግብ​ፅም ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን ሄዱ፤ አዴ​ርም ወደ ፈር​ዖን ገባ። እር​ሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረ​ገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን መጡ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎች ወሰዱ፤ ወደ ግብጽም መጡ፤ ወደ ግብጽም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገቡ፤ እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው፤ ምድርም ሰጠው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 11:18
15 交叉引用  

የሖሪ ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይር በረሓማ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ድረስ ድል አደረጓቸው።


በፋራን ምድረ በዳ ሳለም፣ እናቱ ከግብጽ አንዲት ሴት አምጥታ አጋባችው።


እርሷም፦ ዘምራንን፣ ዮቅሳንን፣ ሜዳንን፣ ምድያምን፣ የስቦቅንና ስዌሕን ወለደችለት።


የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።


ሃዳድ ግን ገና በልጅነቱ አባቱን ካገለገሉ ጥቂት ኤዶማውያን ጋራ ወደ ግብጽ ሸሸ፤


ፈርዖንም ሃዳድን እጅግ ወደደው፤ ስለዚህም ከሚስቱ ከንግሥት ጣፍኔስ እኅት ጋራ አጋባው።


ፈርዖንም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፤ ሙሴ ግን ከፈርዖን ሸሽቶ ወደ ምድያም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ በአንድ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ።


አምላክ ከቴማን፣ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ሴላ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ውዳሴውም ምድርን ሞላ።


ከዚያም እስራኤላውያን ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው ደመናው በፋራን ምድረ በዳ እስኪያርፍ ድረስ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ ተጓዙ።


ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣


ከምድያማዊቷ ሴት ጋራ የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር።


ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለ ሠሩባችሁ ነው።”


ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ።


ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ዓረባ በተባለው ምድረ በዳ ከሱጵ ትይዩ፣ በፋራንና በጦፌል፣ በላባን፣ በሐጼሮትና በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፣ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋራ መጣ፤ በስተ ቀኙ የሚነድድ እሳት ነበር።


跟着我们:

广告


广告