1 ነገሥት 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አባቱም፣ “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ ገሥጾት አያውቅም ነበር፤ አዶንያስም እጅግ መልከ መልካምና የአቤሴሎም ታናሽ ወንድም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አባቱም በሕይወቱ ሳለ፦ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ ከቶ ተቆጥቶት አያውቅም ነበር። ደግሞም መልከ መልካም ነበር፤ የተወለደውም ከአቤሴሎም በኋላ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አባቱም፥ “ከቶ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ አልከለከለውም ነበር፤ እርሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እርሱንም ከአቤሴሎም በኋላ ወልዶት ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አባቱም ከቶ በሕይወቱ ሳለ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ አልተቆጣውም ነበር፤ እርሱ ደግሞ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ ከአቤሴሎምም በኋላ ተወልዶ ነበር። 参见章节 |