Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:52 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ሰሎሞንም፦ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፥ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደሆነ ይሞታል” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ንጉሥ ሰሎሞንም “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጒሩ አንዲት እንኳ አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል” ሲል መለሰ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ሰሎ​ሞ​ንም፥ “እርሱ አካ​ሄ​ዱን ያሳ​መረ እንደ ሆነ ከእ​ርሱ አን​ዲት ጠጕር እንኳ በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተ​ገ​ኘ​በት እንደ ሆነ ይሞ​ታል” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ሰሎሞንም “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል፤” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:52
11 交叉引用  

እርሷም፣ “ደም ተበቃዮቹ ልጄን በማጥፋት የባሰ ጕዳት እንዳያደርሱ፣ ንጉሡ አምላኩን እግዚአብሔርን ይለምን” አለች። ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ከልጅሽ ራስ ላይ አንዲት ጠጕር እንኳ አትነካም” አላት።


ከዚያም፣ ለሰሎሞን፣ “አዶንያስ እነሆ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በመፍራት የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ተማጥኗል፤ እርሱም፣ ‘ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለው ንጉሡ ሰሎሞን ዛሬውኑ ይማልልኝ’ ብሏል” ብለው ነገሩት።


ከዚያም ንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ልኮ ከመሠዊያው ላይ አወረዱት። አዶንያስም መጥቶ ለንጉሥ ሰሎሞን አጐንብሶ እጅ ነሣ፤ ሰሎሞንም፣ “በል ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።


ከጨለማ ወጥቶ ማምለጥ ይፈራል፤ ለሰይፍም የተመደበ ነው።


ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።


ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።


የራስ ጠጕራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው።


ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጕር አንዷ እንኳ አትጠፋም፤


ስለዚህ፣ ለደኅንነታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።”


ሕዝቡ ግን ሳኦልን፣ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? አይደረግም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።


跟着我们:

广告


广告