1 ነገሥት 1:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም51 ከዚያም፣ ለሰሎሞን፣ “አዶንያስ እነሆ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በመፍራት የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ተማጥኗል፤ እርሱም፣ ‘ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለው ንጉሡ ሰሎሞን ዛሬውኑ ይማልልኝ’ ብሏል” ብለው ነገሩት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)51 ለሰሎሞንም፦ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባርያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ’ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም51 ሰዎቹም ሰሎሞንን “አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ‘ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ’ በማለት እየተማጠነ ነው” ሲሉ ነገሩት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)51 ለሰሎሞንም፥ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎሞን አገልጋዩን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)51 ለሰሎሞንም “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ፤’ ብሎ የመሠዊያውን ቀን ይዞአል፤” አሉት። 参见章节 |