1 ቆሮንቶስ 7:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሷልና፤ ያላመነችም ሚስት በሚያምን ባሏ ተቀድሳለች፤ አለዚያማ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፤ ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች፤ እንደዚህ ካልሆነ ግን፥ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ እንደዚህ ከሆነ ግን የተቀደሱ ናቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ክርስቲያን ያልሆነ ባል ክርስቲያን በሆነች ሚስቱ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ይሆናል፤ ክርስቲያን ያልሆነች ሚስትም ክርስቲያን በሆነው ባልዋ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ትሆናለች፤ እንደዚህ ካልሆነማ ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ሊሆኑ አይችሉም፤ በዚህ ዐይነት ከኖራችሁ ግን ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። 参见章节 |