1 ቆሮንቶስ 5:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቷችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ ልታዝኑ አይገባችሁም? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እናንተም ከዚህ ጋር ትዕቢተኞች ናችሁ፤ ይልቁንም ይህን ያደረገው ከእናንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላዘናችሁበትም? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። 参见章节 |