1 ዜና መዋዕል 9:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 መግቢያ በሮቹን በኀላፊነት እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቧቸው ዳዊትና ባለራእዩ ሳሙኤል ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የመግቢያው ደጅ ጠባቂዎች እንዲሆኑ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 መግቢያ በሮችንና ቅጽር በሮችን ለመጠበቅ የተመረጡ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሚኖሩባቸው መንደሮች መሠረት ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ የእነርሱን የቀድሞ አባቶች በዚህ ኀላፊነት የመደቡአቸው ንጉሥ ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ነበሩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ታማኝነታቸውን አይተው በሥራቸው አቆሙአቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። 参见章节 |