Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 7:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እንዲሁም በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤት-ሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የምናሴ ዘሮች ቤትሻንን፥ ታዕናክን፥ መጊዶንና ዶርን እንዲሁም በእነርሱ ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች በቊጥጥራቸው ሥር አድርገው ነበር። እነዚህ ሁሉ የያዕቆብ ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩባቸው የነበሩ ስፍራዎች ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በም​ና​ሴም ልጆች ዳርቻ ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ታዕ​ና​ክና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጊ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በላ​ድና መን​ደ​ሮ​ችዋ ነበሩ፤ በእ​ነ​ዚህ ያዕ​ቆብ የተ​ባለ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ የዮ​ሴፍ ልጆች ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 7:29
12 交叉引用  

የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክና በመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎ ቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለው በቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምን ተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣


ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።


ኢዮስያስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ የአሦርን ንጉሥ ለመርዳት ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጥቶ ነበር፤ ንጉሥ ኢዮስያስም ጦርነት ሊገጥመው ወጣ፤ ሆኖም ፈርዖን ኒካዑ ፊት ለፊት ገጥሞት መጊዶ ላይ ገደለው።


የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ይህን ሲያይ፣ ወደ ቤት ሀጋን በሚያወጣው መንገድ ሸሸ፤ ኢዩም እያሳደደ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እርሱንም ግደሉት!” አለ። እነርሱም በይብለዓም ከተማ አጠገብ በጉር ዐቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቈሰሉት፤ እርሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሽቶ፤ እዚያው ሞተ።


ኢዮስያስ ግን ሌላ ሰው መስሎ በጦርነት ሊገጥመው ወጣ እንጂ ወደ ኋላ አልተመለሰም፤ በመጊዶ ሜዳ ላይ ሊዋጋው ሄደ እንጂ፣ ኒካዑ ከእግዚአብሔር ታዝዞ የነገረውን ሊሰማ አልፈለገም።


በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ ለሐዳድሪሞን እንደ ተለቀሰ ሁሉ በኢየሩሳሌም የሚለቀሰውም እንደዚሁ ታላቅ ልቅሶ ይሆናል።


እነርሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው።


“ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።


የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ ጣዖት ውስጥ አስቀመጡት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤትሳን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።


跟着我们:

广告


广告