Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 6:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋራ ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አገልጋዮቹና ልጆቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚህ ቦታ ተመድበው የሚያገለግሉት ሰዎች የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦ የቀዓት ጐሣ፦ የመጀመሪያው የመዘምራን ቡድን መሪ ኢዩኤል ልጅ ዘማሪው ሄማን ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ያዕቆብ ይደርሳል፦ ሄማን፥ ዮኤል፥ ሳሙኤል፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 6:33
17 交叉引用  

ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ ከወንድሞቻቸው ከሜራሪ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤


መዘምራኑ ኤማን፣ አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤


እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።


አራቱ ሺሕ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺሕ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።


የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ።


እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።


የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣ የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ፣


ከኤማን ዘሮች፣ ይሒኤልና ሰሜኢ፣ ከኤዶታም ዘሮች፣ ሸማያና ዑዝኤል።


መዘምራን የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፣ አሳፍ፣ ኤማን፣ ሄማንና ኤዶታም፣ ወንዶች ልጆቻቸውና የሥጋ ዘመዶቻቸው ሁሉ ያማረ ቀጭን በፍታ ለብሰው፣ ከመሠዊያው በስተምሥራቅ በኩል ቆመው ጸናጽል ይጸነጽሉ፣ በገና ይደረድሩና መሰንቆ ይመቱ ነበር፤ እነርሱም መለከት በሚነፉ አንድ መቶ ሃያ ካህናት ታጅበው ነበር።


አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።


“የሌዊን ነገድ አምጥተህ ካህኑን አሮንን በአገልግሎቱ እንዲረዱት ከፊቱ አቁማቸው፤


ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ተለይተው ለርሱ ፈጽመው የተሰጡ ናቸው።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ የኤያሬምኤል ልጅ፣ የኢሊዩ ልጅ፣ የቶሑ ልጅ፣ የናሲብ ልጅ፣ ነበረ።


ስለዚህ ሐና ፀነሰች፤ የእርግዝናዋ ወራት በተፈጸመ ጊዜም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም፤ “ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ሳሙኤል አለችው።


ስለዚህ እኔም ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገደ።


跟着我们:

广告


广告