Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 3:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሦስተኛው አቤሴሎም የመዓካ ልጅ እርሷም የጌሹር ንጉሥ የተልማይ ልጅ ነበረች፥ አራተኛው አዶንያስ የአጊት ልጅ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 3:2
20 交叉引用  

የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቈንጆ እኅት ነበረችው፤ እርሷንም የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት።


አቤሴሎም ሸሽቶ ወደ ጌሹር ከሄደ በኋላ፣ በዚያ ሦስት ዓመት ተቀመጠ።


ከዚያም ኢዮአብ ወደ ጌሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው።


አቤሴሎምም፣ ኢዮአብን፣ “ከጌሹር ለምን መጣሁ? ‘ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና’ ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን፤ የንጉሡን ዐይን ማየት እፈልጋለሁ፤ ምንም ዐይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው።


እኔ አገልጋይህ በሶርያ ምድር በጌሹር ሳለሁ ‘እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም የመለሰኝ እንደ ሆነ፣ በኬብሮን ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስያለሁ።”


ኢዮአብም፣ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋራ ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ፣ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።


አቤሴሎም፣ “ስሜን የሚያስጠራ ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ በራሱ ስም ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፣ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።


ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር።


ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ፣ ሦስተኛው፣ ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣


አራተኛው፣ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ ዐምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣


በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ ዐምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።


አባቱም፣ “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ ገሥጾት አያውቅም ነበር፤ አዶንያስም እጅግ መልከ መልካምና የአቤሴሎም ታናሽ ወንድም ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞንም እናቱን፣ “ስለ ምን ሱነማዪቱን አቢሳን ብቻ ለአዶንያስ ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ስለ ሆነ መንግሥቱንም ጠይቂለት እንጂ፤ ለርሱ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም ለካህኑ ለአብያታርና ለጽሩያ ልጅ ለኢዮአብ ጠይቂላቸው” አላት።


ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።


ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣ ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣


ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።


ነገር ግን እስራኤላውያን የጌሹርንና የማዕካትን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላቸው ይኖራሉ።


跟着我们:

广告


广告