Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 29:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከርሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጐናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጌታም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር በአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰሎሞንን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከዚህ በፊት እስራኤልን ከገዛ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ የተከበረ እንዲሆንም አደረገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 29:25
13 交叉引用  

እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋራ እንደ ነበረ ሁሉ፣ ከሰሎሞንም ጋራ ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው።”


ይህንኑ አደርግልሃለሁ፤ ከአንተ በፊት ማንም ያልነበረውን፣ ከአንተም በኋላ ማንም የማያገኘውን ጥበብና አስተዋይ ልቡና እሰጥሃለሁ፤


ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅኸውን ብልጽግናና ክብር እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በሕይወት ዘመንህ የሚተካከልህ ማንም ንጉሥ እንዳይኖር ነው።


የጦር አለቆቹና ኀያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሡ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋገጡለት።


አምላኩ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበር፣ እጅግም ስላገነነው፣ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በመንግሥቱ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ።


ጥበብና ዕውቀት ይሰጥሃል፤ እንዲሁም ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተ በኋላም የሚነሣው የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”


“ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፣ ልብህንም ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድን ነው?


ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሆንሁ፤ በዚህ ሁሉ ጥበቤ ከእኔ ጋራ ነበረች።


ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት፣ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ሁሉ ዘንድ በታወቀ ጊዜ፣ ሁሉም ፍርሀት ያዛቸው፤ በዚህም የጌታ የኢየሱስ ስም ተከበረ።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።


እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ከሙሴ ጋራ እንደ ነበርሁ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ መሆኔን ያውቁ ዘንድ፣ በእስራኤል ሁሉ ፊት አንተን ከፍ ከፍ ማድረጌን በዛሬዋ ዕለት እጀምራለሁ።


በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት።


跟着我们:

广告


广告