1 ዜና መዋዕል 29:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በዚያችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህናቸው እንዲሆን ቀቡት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በጌታ ፊት በሉ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም ልዑል እንዲሆን ለጌታ ቀቡት፥ ሳዶቅንም ካህን እንዲሆን ቀቡት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ስለዚህ በዚያን ቀን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ እጅግ ደስ ተሰኙ። ለሁለተኛ ጊዜም ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን አረጋገጡ፤ በእግዚአብሔር ስም ቀብተው ንጉሣቸው አደረጉት፤ ሳዶቅንም ቀብተው ካህናቸው አደረጉት፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀቡት፤ ሳዶቅም በካህናት ላይ ተሾመ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሔር ፊት በሉ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም አለቃ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህን ይሆን ዘንድ ቀቡት። 参见章节 |