Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 28:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንዲህም አለኝ፤ ‘ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጬዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ልጅ እንዲሆንልኝ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔርም “ ‘ቤተ መቅደሴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ እርሱ እንደ ልጄ ይሆናል፤ እኔም እንደ አባት እሆነዋለሁ’ ብሎኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆ​ነኝ ዘንድ መር​ጬ​ዋ​ለ​ሁና፥ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለ​ሁና ልጅህ ሰሎ​ሞን ቤቴ​ንና አደ​ባ​ባ​ዮ​ቼን ይሠ​ራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እርሱም ‘ልጅ ይሆንልኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 28:6
11 交叉引用  

እነሆ፣ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአንተ ቀጥሎ በዙፋንህ የማስቀምጠው ልጅህ ነው’ ብሎ እንደ ነገረው፣ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት ዐስቤአለሁ።


“እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጽሟል፤ እኔም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ።


አሁን እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ያነገሥኸኝ ብዛቱ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ሕዝብ ላይ ስለ ሆነ፣ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና።


በመግቢያው በር ዙሪያ ባሉት ወጣ ወጣ ባሉት ግንቦች ሁሉ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ለካ፤ ስድሳ ክንድም ነበር። የተለካውም ከአደባባዩ ፊት ለፊት እስካለው መተላለፊያ በረንዳ ድረስ ነበር።


ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቷል።


ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።


ቀደም ባለው ክፍል ደግሞ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።


跟着我们:

广告


广告