Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 26:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ንጉሥ ዳዊት ከእነዚያ ዘመዶች መካከል ምርጥ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ የቤተሰብ አለቆችን መረጠ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ማለትም በሮቤል፥ በጋድና በምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛቶች መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ጉዳይ ሁሉ የማስተዳደር ኀላፊነት ሰጣቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ወን​ድ​ሞ​ቹም ጽኑ​ዓን የነ​በ​ሩት የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁሉና በን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያ​ንና በጋ​ዳ​ው​ያን፥ በም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ላይ ሹሞች አደ​ረ​ጋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኵሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 26:32
7 交叉引用  

ከምሥራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺሕ ሰዎች።


እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ስለ ሆናችሁ፣ እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ ከዚያም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።


እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።


ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።


የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።


“የእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ላይ የካህናቱ አለቃ አማርያ፣ የንጉሡ በሆነው ነገር ሁሉ ላይ የይሁዳ ነገድ መሪ የሆነው የእስማኤል ልጅ ዝባድያ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ሆነው ያገለግላሉ፤ በርትታችሁ ሥሩ፤ እግዚአብሔርም መልካም ከሚያደርጉ ጋራ ይሁን።”


ኢያሱ የሮቤልን ነገድ፣ የጋድን ነገድና የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤


跟着我们:

广告


广告