Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 25:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እነዚህም ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ የሚያደርጉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር የንጉሡ ነቢይ ለሆነው ለሄማን እነዚህን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆችን ጭምር ሰጠው፤ ይህንንም ያደረገው የሄማንን ኀይል ከፍ ለማድረግ ቀደም ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነ​ዚህ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ቱን ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በን​ጉሡ ፊት የሚ​ዘ​ም​ረው የኤ​ማን ልጆች ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኤ​ማን ዐሥራ አራት ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ሦስት ሴቶች ልጆ​ችን ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራዕይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 25:5
9 交叉引用  

ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ ዐብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።


በማግስቱም ጧት ዳዊት ከመነሣቱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል የዳዊት ባለራእይ ወደ ሆነው ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ መጣ፤


እግዚአብሔርም የዳዊት ባለራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤


ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።


እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።


መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር።


እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።


እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።


ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፣ “ኑ ወደ ባለራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለራእይ ይባል ነበርና።


跟着我们:

广告


广告