Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 24:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተ ሰብ አለቆች፤ ከኢታምርም ዘሮች ስምንት የቤተ ሰብ አለቆች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የአልዓዛር ቤተሰብ ቊጥር ከኢታማር ቤተሰብ ቊጥር በልጦ ስለ ተገኘ አመዳደቡም በዚሁ መሠረት ተወሰነ፤ ስለዚህ የአልዓዛር የቤተሰብ አለቆች ቊጥር ዐሥራ ስድስት ሆኖ ሲደለደል የኢታማር አለቆች ቊጥር ስምንት እንዲሆን ወሰነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የአ​ል​ዓ​ዛ​ርም ልጆች አለ​ቆች ከኢ​ታ​ምር ልጆች አለ​ቆች በል​ጠው ተገኙ፤ እን​ዲ​ህም ተመ​ደቡ፤ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ዐሥራ ስድ​ስት አለ​ቆች፥ ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ስም​ንት አለ​ቆች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 24:4
7 交叉引用  

እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።


ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው።


ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።


ከዚያም ሰሎሞን ለመላው እስራኤል፣ ለሻለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለዳኞች፣ ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንዲሁም ለየቤተ ሰቡ አለቆች ተናገረ።


በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤


跟着我们:

广告


广告