Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 23:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የጌታን ቤት አገልግሎት በሠሩ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመትና ከዚያም ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 23:24
20 交叉引用  

የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ለኢያሪሙት በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።


ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።


ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺሕ ነበረ።


በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።


ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር፣ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ እንዲሁም የቀሩት ወንድሞቻቸው (ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ሁሉ) ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤት ሕንጻ ሥራ እንዲቈጣጠሩ ሾሟቸው፤ ሥራውንም ጀመሩ።


ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።


ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤


ከስምዖን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።


ከዚህ በኋላ ማደሪያው ተነቀለ፤ ድንኳኑን የተሸከሙት ጌርሶናውያንና ሜራሪያውያንም ጕዞ ጀመሩ።


ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።


“በእስራኤላውያን ላይ ዳግም ቍጣ እንዳይደርስባቸው የመቅደሱና የመሠዊያው እንክብካቤ ኀላፊነት የሚመለከተው እናንተን ይሆናል።


በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ናቸው፤


“ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።


የሜራሪ ጐሣዎች፤ ሞሖሊና ሙሲ። እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው።


ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ ዐምስት ዐምስት ሰቅል ተቀበል፤


ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ወንዶች ሁሉ ቍጠር።


እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቍጠሩ።


“ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤


跟着我们:

广告


广告