Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፣ “ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላውያን ቍጠሩ፤ ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ “ሂዱ፥ ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቁጠሩ፥ ድምራቸውንም እንዳውቅ ተመልሳችሁ አስታውቁኝ” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዳዊት ለኢዮአብና ለሌሎቹ የጦር መኰንኖች “በመላው እስራኤል ከአገሪቱ ዳር እስከ ዳር፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሄዳችሁ ሕዝቡን ቊጠሩ፤ እኔ በእስራኤል ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ እፈልጋለሁ” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ፥ “ሂዱ፥ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስ​ራ​ኤ​ልን ቍጠሩ፤ ድም​ራ​ቸ​ው​ንም አውቅ ዘንድ አስ​ታ​ው​ቁኝ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች “ሂዱ፤ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፤ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ፤” አላቸው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:2
14 交叉引用  

በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።


“እንግዲህ እኔ የምመክርህ ይህ ነው፤ ቍጥሩ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛው፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ ይሰብሰብና አንተው ራስህ ወደ ጦርነቱ ምራው፤


ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚያች ዕለት ጧት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ።


የማለለትም መንግሥትን ከሳኦል ቤት አውጥቶ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት የሰጠው ተስፋ ነው።”


በሰሎሞን ዘመን ሁሉ ከዳን አንሥቶ እስከ ቤርሳቤህ ያለው ይሁዳና እስራኤል፣ እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ ጥላ ሥር ያለ ሥጋት ለመኖር በቃ።


ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ሕዝቡ ከመላው ኢየሩሳሌም እንዲመጣ፣ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ ዐዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉ ብዛት ባለው ሕዝብ ተከብሮ አያውቅም ነበርና።


ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።


ከዚህ ታላቅ መገለጥ የተነሣ እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም የሚያሠቃየኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ።


ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ።


ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል በርግጥ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።


跟着我们:

广告


广告