Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 20:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያ የነበረውንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው። ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረገ። ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በውስጥዋም የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በመጥረቢያም እንዲሠሩ አደረጋቸው። እንዲሁም ዳዊት በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የከተማይቱንም ሕዝብ ማርኮ በመጋዝ፥ በዶማና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ በዐሞን በሚገኙ በሌሎች ታናናሽ ከተማዎች የሚኖሩትንም ሰዎች በዚሁ ዐይነት እንዲሠሩ አደረገ፤ ከዚያም በኋላ እርሱና ሠራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥተው በመ​ጋዝ ተረ​ተ​ሩ​አ​ቸው፤ በመ​ጥ​ረ​ቢ​ያም ቈራ​ረ​ጡ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በውስጥዋም የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በመጥረቢያም እንዲሠሩ አደረጋቸው። እንዲሁም ዳዊት በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 20:3
9 交叉引用  

እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ የብረት መቈፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፣ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በሌሎቹ የአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሰራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።


ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በዕርሻም ሁሉ እያስጨነቁ ከባድ ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን አስመረሩ፤ ግብጻውያኑ በሚያሠሯቸው ከባድ ሥራ ሁሉ ፈጽሞ አይራሩላቸውም ነበር።


በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤


ስለዚህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ ጥቂቶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ምን ጊዜም ዕንጨት ቈራጭ፣ ውሃ ቀጂ ባሮች ትሆናላችሁ።”


跟着我们:

广告


广告