Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣሄል ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች፤ አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ናቸው፤ ሦስቱ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢጌል ይባሉ ነበር፤ የጽሩያም ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳይ፥ ኢዮአብና ዓሣሄል ተብለው ይጠሩ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሶር​ህ​ያና አቢ​ግያ ነበሩ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮ​አብ፥ አሣ​ሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ሦስቱ ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 2:16
11 交叉引用  

የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ።


አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር።


ዳዊትም፣ “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ እናንተንና እኔን ምን የሚያገናኘን ነገር አለ? ዛሬ ጠላት ሆናችሁኛል! ማንስ ቢሆን ዛሬ በእስራኤል ዘንድ ሰው መሞት አለበት? እኔ በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅሁበት ቀን አይደለምን?” ብሎ መለሰ።


እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኵሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ አንዱ ወገን በኵሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኵሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።


ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”


የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።


ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።


አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።


ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፣ “ወደ ሳኦል ሰፈር ዐብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፣ “እኔ ዐብሬህ እወርዳለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告