1 ዜና መዋዕል 19:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ወደ ፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ። ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤ እነርሱም ተዋጉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ ለውግያ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ዳዊት ስለዚህ ነገር በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን የጦር ኀይል ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ የውጊያ መስመሩን ያዘ፤ ሶርያውያንም እንደዚሁ ቦታቸውን ይዘው ከዳዊት ጋር ጦርነት ገጠሙ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ዳዊትም በተነገረው ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ጋር ተዋጋ፥ እነርሱም ከእርሱ ጋር ተዋጉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፤ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ። 参见章节 |