Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚህም በላይ ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት ለመቈጣጠር በሄደ ጊዜ፣ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ ዘልቆ ወጋው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት ለመያዝ በሄደ ጊዜ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ መታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት በሶርያ አገር እስከ ሐማት ግዛት አጠገብ በምትገኘው በጾባ ንጉሥ በሀዳድዔዜር ላይ አደጋ ጣለ፤ ይህንንም ያደረገው ሀዳድዔዜር ከላይ በኩል በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዘምቶ ስለ ነበር ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት ለመያዝ በሄደ ጊዜ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ መታ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:3
11 交叉引用  

በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤


አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።


ከዚህም በቀር ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፣ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ወጋው።


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ እነርሱም ገባሮቹ ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።


ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገላ፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኛና ሃያ ሺሕ እግረኛ ወታደር ማረከ፤ አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቈረጠ።


ከዚያም ሰሎሞን ወደ ሐማት ሱባ ዘመተ፤ ያዛትም።


ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።


ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤ ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።


“ድንበርህን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ።


ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


跟着我们:

广告


广告