Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እጅ እንዲነሣውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዶራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር። አዶራምም ከወርቅ፣ ከብርና ከናስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ድል ስለ አደረገው ደኅንነቱን እንዲጠይቀውና እንዲመርቀው ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት አድርጎ ስለ ነበር፥ ንጉሥ ዳዊትን እጅ እንዲነሣና በሀዳድዔዜር ላይ ስለ ተቀዳጀው ድል ደስታውን እንዲገልጥለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከ። ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ገጸ በረከት አድርጎ ለዳዊት አመጣለት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ስለ መታው ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ ይመርቀው ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:10
6 交叉引用  

ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ስለ ተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።


ንጉሥ ዳዊት ከኤዶምና ሞዓብ፣ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጥኤማውያንና ከአማሌቃውያን፣ ከእነዚህ ሁሉ መንግሥታት የማረከውን ወርቅና ብር ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ፣ እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሰ።


የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደ መታ ሲሰማ፣


የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። ቅመማ ቅመም፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋራ ደረሰች፤ ወደ ሰሎሞንም ቀርባ በልቧ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።


በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።


跟着我们:

广告


广告