Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 17:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አሁንም ባርያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ እንድትሆን አንተን ከማሰማርያው፥ ከበግ እረኝነት ወሰድሁህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ስለዚህ እኔ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለአገልጋዬ ለዳዊት የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከበግ እረኝነት አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዬን ዳዊ​ትን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ መን​ጋ​ውን ስት​ከ​ተል በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰ​ድ​ሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 17:7
13 交叉引用  

ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ከአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በእግዚአብሔር ፊት አሸብሽቤአለሁ፤ አሁንም አሸበሽባለሁ።


“አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤


በእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ባለፍሁባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ካዘዝኋቸው መሪዎቻቸው “ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሠራችሁልኝም” ያልሁት አለን?’


በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁም፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ፤ አሁንም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።


አሁን ግን ስሜ በዚያ እንዲሆን ኢየሩሳሌምን፣ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲገዛም ዳዊትን መርጫለሁ።’


“ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከሌሎቹ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤ የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ ከአንቺ ይወጣልና።’ ”


ደግሞም የስምዖን ባልንጀሮች የነበሩት የዘብዴዎስ ልጆች፣ ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፣ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው።


ዳዊት ግን የአባቱን በጎች ለመጠበቅ ከሳኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመላለስ ነበር።


跟着我们:

广告


广告