Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 17:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እስራኤልን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱ ማደሪያ ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖሬ አላውቅም፤ ዘወትር በድንኳን ውስጥ ሆኜ ከቦታ ወደ ቦታ እዘዋወር ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አል​ኖ​ር​ሁም።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 17:5
12 交叉引用  

ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው፣ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ።


እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።


‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንሥቶ፣ ስሜ በዚያ እንዲጠራና ቤተ መቅደስ እንዲሠራበት ከመላው የእስራኤል ነገድ አንድም ከተማ አልመረጥሁም፤ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲመራ ግን ዳዊትን መረጥሁት።’


“ነገር ግን አምላክ በርግጥ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማይ፣ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ እንኳ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የመገናኛውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አመጡ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ተሸከሟቸው።


ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ እንኳ እርሱን ይይዘው ዘንድ አይችልምና ቤተ መቅደስ ሊሠራለት የሚችል ማነው? በፊቱ ዕጣን የሚታጠንበትን እንጂ ቤተ መቅደስ እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?


“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋራ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማያትና ሰማየ ሰማያት እንኳ አንተን ሊይዙህ አይችሉም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ ይሠራበት ዘንድ ከማናቸውም የእስራኤል ነገድ ከተሞች አንድም አልመረጥሁም፤ ወይም የሕዝቤ የእስራኤል መሪ ይሆን ዘንድ ማንንም አልመረጥሁም።


አሁን ግን ስሜ በዚያ እንዲሆን ኢየሩሳሌምን፣ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲገዛም ዳዊትን መርጫለሁ።’


跟着我们:

广告


广告