1 ዜና መዋዕል 17:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 “ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 “ሂድ፥ ለባርያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 “ወደ አገልጋዬ ወደ ዳዊት ሄደህ እንዲህ በለው ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 “ሂድ፥ ለአገልጋዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጡ እኖርበት ዘንድ ቤትን የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4-5 “ሂድ፤ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም። 参见章节 |