1 ዜና መዋዕል 16:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከርሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ ከዚያም ይዒኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ መቲትያ፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ አቢዳራ፣ ይዒኤል ተሾሙ፤ እነርሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤ አሳፍ ደግሞ ጸናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 አሳፍ መሪ፥ ዘካርያስም የእርሱ ረዳት ሆነው ተሾሙ፤ ይዒኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ማቲትያ፥ ኤሊአብ፥ በናያ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል መሰንቆና በገና ለመደርደር፥ አሳፍም ጸናጽል ለማንሿሿት ተመደቡ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 አለቃውም አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዘካርያስ፥ ኢያሔል፥ ሰሜራሞት፥ ይሔኤል፥ ማታትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ አብዲዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና፥ አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር። 参见章节 |