1 ዜና መዋዕል 14:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣ “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈራረሳቸው” አለ፤ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ስለዚህ ዳዊት ባዓልፈራጺም ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ ድል ካደረጋቸው በኋላ “የጠላትን ሠራዊት እንደ ጐርፍ ጥሼ እንዳልፍ እግዚአብሔር ረዳኝ” አለ፤ ከዚያም በኋላ ያ ስፍራ “ባዓልፈራጺም” ተብሎ ተጠራ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ወደ በኣልፐራሲምም ወጡ፤ በዚያም ዳዊት መታቸው። ዳዊትም “ውሃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው፤” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም “በኣልፐራሲም” ብለው ጠሩት። 参见章节 |