Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 13:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከቂርያትይዓይሪም ለማምጣት ከግብጽ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ለቦ ሐማት ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያት-ይዓሪም ለማምጣት ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ከሺሆር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቂርያትይዓሪም ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደቡብ በኩል እስከ ግብጽ ግዛት ድንበር፥ በሰሜን እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ በመላው እስራኤል የሚገኘውን ሕዝብ በአንድነት ሰበሰበ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ሰበ​ሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ከሺሆር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 13:5
16 交叉引用  

ዳዊት እንደ ገና ከእስራኤል የተመረጡ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ ሰዎች ሰበሰበ።


ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብጽ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።


በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋራ በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ።


ንጉሡም ሰዎቹን በሐማት ምድር በነበረችው በሪብላ ውስጥ አስገደላቸው። ይሁዳም ከምድሩ በዚህ ሁኔታ ተማርኮ ሄደ።


ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።


ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በኪሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን ስሙም በርሱ የተጠራውን፣ የእግዚአብሔር አምላክን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓይሪም ወደተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።


ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


በታላላቅ ውሆች ላይ፣ ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤ የአባይ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።


ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣ አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ? ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?


ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ።


ከዚያም ወደ ቂርያትይዓይሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፣ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰውልናል፤ ውረዱና ይዛችሁ ወደ ሰፈራችሁ ውጡ” አሏቸው።


የቂርያትይዓይሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኰረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።


ታቦቱ በቂርያትይዓይሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ በአጠቃላይ ሃያ ዓመት ቈየ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም ፈለገ።


跟着我们:

广告


广告