Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 12:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 የሚያስፈልጋቸውንም ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለ ነበር፣ ሰዎቹ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋራ ሦስት ቀን ቈዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ወንድሞቻቸውም አዘጋጅተውላቸው ነበርና እየበሉና እየጠጡ በዚያ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 እነዚህ ሁሉ የገዛ ወገኖቻቸው ያዘጋጁላቸውን በደስታ እየተመገቡና እየጠጡ፥ ሦስት ቀን ከዳዊት ጋር ቈዩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ው​ላ​ቸው ነበ​ርና እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ በዚያ ከዳ​ዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ወንድሞቻቸውም አዘጋጅተውላቸው ነበርና እየበሉና እየጠጡ በዚያ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀመጡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 12:39
8 交叉引用  

ይሥሐቅም ድግስ ደግሶ አበላቸው፤ አጠጣቸው።


ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው ዐደሩ።


በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዢነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል። ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።


የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፣ ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለ ሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቈጣ ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሏቸው።


የእስራኤል ወገን ለሆነው ለሕዝቡ ሁሉ፣ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣ አንዳንድ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ ሰጠ፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም ወደየቤቱ ሄደ።


የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።


እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው። ወደ ኬብሮን የመጡትም ዳዊትን በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው። የቀሩትም እስራኤላውያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።


እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ ከዛብሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ስለ ሆነ ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።


跟着我们:

广告


广告