Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 12:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፣ የሳኦልን መንግሥት አንሥተው ለርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ኬብሮን የመጡት ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እንደ ጌታም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ለመመለስ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23-37 ዳዊት በኬብሮን ሳለ ብዙ የሠለጠኑ ወታደሮች ወደ እርሱ ሠራዊት ገቡ፤ እግዚአብሔር በሰጠውም የተስፋ ቃል መሠረት በሳኦል እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ብዙ ርዳታ አደረጉለት፤ ቊጥራቸውም እንደሚከተለው ነበር፦ ከይሁዳ ነገድ፦ ጋሻና ጦር በሚገባ የታጠቁ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ወታደሮች፥ ከስምዖን ነገድ፦ በሚገባ የሠለጠኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ወታደሮች፥ ከሌዊ ነገድ፦ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት የዮዳሄ ተከታዮች ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ታዋቂ ጦረኛ ከሆነው ከጻዶቅ ዘመዶች፦ ኻያ ሁለት የጦር አዛዦች፥ የሳኦል ወገን ከሆነው ከብንያም ነገድ፦ ሦስት ሺህ ሰዎች፤ ይሁን እንጂ ከብንያም ነገድ አብዛኛው ሕዝብ ለሳኦል ያላቸውን ታማኝነት እንደ ቀጠሉ ነበሩ። ከኤፍሬም ነገድ፦ ኻያ ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሆኑ፥ ሁሉም በየጐሣቸው ዝነኞች የሆኑ ጀግኖች ነበሩ። በምዕራብ በኩል ካለው ከምናሴ ነገድ፦ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በተለይ የተመረጡ ናቸው። ከይሳኮር ነገድ፦ ሁለት መቶ መሪዎች ሲሆኑ፥ በእነርሱ አመራር ሥር ያሉትንም ያጠቃልላል፤ እነዚህ መሪዎች እስራኤል ምን ማድረግና መቼ ማድረግ እንደሚገባት የሚያውቁ ናቸው። ከዛብሎን ነገድ፦ እምነት የሚጣልባቸው ለጦርነት ዝግጁዎች የሆኑ በማንኛውም መሣሪያ መጠቀም የሚችሉ ኀምሳ ሺህ ወታደሮች፤ ከንፍታሌም ነገድ፦ አንድ ሺህ የጦር መሪዎችና ጋሻና ጦር ያነገቡ ሠላሳ ሰባት ሺህ ወታደሮች ነበሩ። ከዳን ነገድ፦ ኻያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ የሠለጠኑ ወታደሮች ነበሩ። ከአሴር ነገድ፦ አርባ ሺህ ለጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች ነበሩ። ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ካሉት ከሮቤል፥ ከጋድና ከምናሴ ነገዶች፦ በማንኛውም ዐይነት መሣሪያ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው አንድ መቶ ኻያ ሺህ ወታደሮች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሳ​ኦ​ልን መን​ግ​ሥት ወደ እርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ በኬ​ብ​ሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመ​ጡት የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ቍጥር ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እንደ እግዚአብሔርም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ይመልሱ ዘንድ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 12:23
13 交叉引用  

ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤


እግዚአብሔር ለዳዊት፣ ‘በባሪያዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ተስፋ ስለ ሰጠው፣ ይህን አሁኑኑ አድርጉት።”


ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።


የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።


ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺሕ ስምንት መቶ፤


ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣ በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።


እግዚአብሔር ሳሙኤልን፣ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተ ልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፣ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


እሴይን ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፤ ከዚያም የምታደርገውን አሳይሃለሁ፤ የምነግርህንም ሰው ትቀባልኛለህ።”


跟着我们:

广告


广告