Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 11:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚያም፣ “ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ፤ ይህ በሕይወታቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?” አለ። ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቈርጠው ስለ ነበር፣ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱም እንዲህ አለ፦ “ይህን እንዳደርግ አምላኬ አይፈቅድልኝም፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው አምጥተውታል።” ስለዚህም ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “እኔ ይህን ውሃ መጠጣት ከቶ አልችልም! እኔ ይህን ውሃ ብጠጣ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚያን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል!” አለ። ስለዚህም ውሃውን ይጠጣ ዘንድ አልወደደም፤ እንግዲህ ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፈጸሙአቸው የጀግንነት ተግባሮች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አም​ላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለሞት አሳ​ል​ፈው አም​ጥ​ተ​ው​ታ​ልና የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ደም እጠ​ጣ​ለ​ሁን?” አለ። ስለ​ዚ​ህም ዳዊት ይጠ​ጣው ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስ​ቱም ኀያ​ላን ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 “ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ይከልክለኝ፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? በነፍሳቸው አምጥተውታል፤” አለ። ስለዚህም ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 11:19
16 交叉引用  

“ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።


“እርሱም፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።


ናቡቴ ግን አክዓብን፣ “ዐፅመ ርስቴን እለቅቅልህ ዘንድ እግዚአብሔር አይበለው” ሲል መለሰለት።


በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጕድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው።


የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።


የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ ያልጠገበ ማን ነው?’ ብለው ካልሆነ፣


ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ ደማቸውም በርሱ ፊት ክቡር ነው።


“ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤


ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤


ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፤


እነርሱም ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሰጡ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል።


እኛስ ብንሆን ዘወትር ለአደጋ የምንጋለጠው ለምንድን ነው?


የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ የንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብቶች አደረጉ።


አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፣ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን ዐሰባችሁ ማለት ነው።


ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቈርጦ ነው። እግዚአብሔር ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”


跟着我们:

广告


广告