Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል ሊያነግሡት ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው፦ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ሆነው እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ዳዊት እንዲነግሥ በጣም ረድተዋል። መንግሥቱም ጽኑና ኀያል እንዲሆን አድርገዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 11:10
13 交叉引用  

ከዚያም አበኔር ዳዊትን፤ “ከአንተ ጋራ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፣ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ሄጄ፣ ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።


ስለዚህ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን ገባ። እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በተናገረው መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።


ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ስለ ነበሩ፣ አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።


እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፣ የሳኦልን መንግሥት አንሥተው ለርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ኬብሮን የመጡት ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤


ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺሕ ስምንት መቶ፤


እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው። ወደ ኬብሮን የመጡትም ዳዊትን በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው። የቀሩትም እስራኤላውያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።


የሚያስፈልጋቸውንም ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለ ነበር፣ ሰዎቹ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋራ ሦስት ቀን ቈዩ።


የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።


ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የከፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሡና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኀላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኀያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።


እግዚአብሔር ሳሙኤልን፣ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተ ልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፣ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告