ዘካርያስ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በዚያን ጊዜ በሩቅ የሚኖሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲታደስ ለመርዳት ይመጣሉ። ቤተ መቅደሱ በታደሰ ጊዜ እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቃላችሁ። ይህም ሁሉ የሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቃል ፍጹም ታዛዦች የሆናችሁ እንደ ሆነ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እነዚያ በሩቅ ያሉት መጥተው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሠራ ያግዛሉ፤ እናንተም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በጥንቃቄ ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል። 参见章节 |