Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 መልአኩም “እነሆ ይህች ሴት የዐመፅ ምሳሌ ነች” ከአለኝ በኋላ ወደ ታች ገፍቶ ወደ ቅርጫቱ ውስጥ አስገባት፤ ክዳኑንም መልሶ ገጠመው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱም፣ “ይህች ርኩሰት ናት” ብሎ ወደ ኢፍ መስፈሪያ መልሶ አስገባት፤ የእርሳሱንም ክዳን ወደ ቅርጫቱ አፍ ገፍቶ ገጠመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እርሱም፦ “ይህች ክፋት ናት” አለኝ፤ ከዚያም በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እርሱም፦ ይህች ክፋት ናት አለኝ፣ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም፦ ይህች ክፋት ናት አለኝ፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ።

参见章节 复制




ዘካርያስ 5:8
11 交叉引用  

የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”


በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤ እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


“በደሎቼ በጫንቃዬ ላይ ታስረዋል፤ እነርሱም በጣም ከባድ ስለ ሆኑ ኀይል አሳጡን፤ ልንቋቋማቸው ለማንችላቸው ጠላቶቻችን አሳልፎ ሰጠን።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ሐሰተኛ ሚዛን በእጃቸው እንደሚገኝ እንደ ከነዓናውያን ነጋዴዎች ሆነዋል፤ በእርሱም ያታልሉበታል፤


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤


ታዲያ በሐሰተኛ ሚዛንና መስፈሪያ የሚጠቀሙትን ሰዎች እታገሣለሁን?


ቅርጫቱ ከእርሳስ የተሠራ መክደኛ ነበረው፤ እኔም እያየሁት መክደኛው ተከፈተ፤ እነሆም በቅርጫቱ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።


እንግዲያውስ አባቶቻችሁ የጀመሩትን እናንተም ፈጽሙ።


አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።


跟着我们:

广告


广告