ዘካርያስ 12:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደ ጋሻ መከታ እሆንላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ እጅግ ደካማ የተባለው እንኳ የዳዊትን ያኽል ብርቱ ይሆናል፤ የዳዊት ልጆች እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ወይም እንደ መላእክት ሆነው ሕዝቡን ይመራሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ከመካከላቸው እጅግ ደካማ የሆነው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም ፊት ፊታቸው እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ አምላክ ይሆንላቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይከልላቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፥ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል። 参见章节 |