Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 8:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርስዋ ቅጽር ብትሆን ኖሮ የብር ማማ እንሠራላት ነበር፤ እርስዋ የቅጽር በር ብትሆን ኖሮ ከሊባኖስ ዛፍ ሳንቃ የታነጸ መዝጊያ እንሠራላት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሷ ቅጥር ብትሆን፣ በላይዋ የብር መጠበቂያ ማማ እንሠራባታለን፤ በር ብትሆን፣ በዝግባ ዕንጨት እንከልላታለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሷ ቅጥር ብትሆን የብር ግንብ በላይዋ እንሠራለን፥ ደጅም ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እንከብባታለን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ስዋ ቅጥር ብት​ሆን የብር ግንብ በላ​ይዋ እን​ሥራ፤ ደጅ​አ​ፍም ብት​ሆን የዝ​ግባ ሳንቃ እን​ሥ​ራ​ላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርስዋ ቅጥር ብትሆን የብር ግንብ በላይዋ እንሠራለን፥ ደጅም ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እንከብባታለን።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 8:9
14 交叉引用  

የቤተ መቅደሱ ግንብ ከውስጥ በኩል ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርበው በተሠሩ ሳንቃዎች ተለበደ፤ የወለሉም ጣውላ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር።


እኛ ግን የብር ፈርጥ ያለው የወርቅ ጌጥ እናሠራልሻለን።


ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤ እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤ በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።


ሕዝባችሁ ቀድሞ ፈራርሰው የነበሩትን ሁሉ እንደገና መልሶ በጥንቱ መሠረት ላይ ይሠራል፤ ስለዚህም እናንተ ‘ቅጽሮችን መልሶ የሚያንጽና ፈራርሰው የነበሩ ቤቶችን የሚያድስ ሕዝብ’ ተብላችሁ ትጠራላችሁ።”


“እኔ በነሐስ ፈንታ ወርቅ፥ በብረት ፈንታ ብር፥ በእንጨት ፈንታ ነሐስ፥ በድንጋይም ፈንታ ብረት አመጣለሁ፤ ሰላምን እንደ አስተዳዳሪሽ ጽድቅንም እንደ ገዢሽ አድርጌ እመድባለሁ።


እነርሱ የጥንት ፍርስራሾችን ይገነባሉ፤ ቀደም ብለው የወደሙትን እንደገና ይሠራሉ፤ በየትውልዱ የፈራረሱትን ከተሞች ያድሳሉ፤


እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።


እዚያም በደረሱ ጊዜ አማኞችን በአንድነት ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉና አሕዛብም እንዲያምኑ እንዴት አድርጎ በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።


‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውንም የዳዊትን ቤት እሠራለሁ፤ ፍርስራሹንም ጠግኜ እንደገና አቆማለሁ።


“አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ በጣራው ክፈፍ ዙሪያ መከታ አድርግለት፤ አለበለዚያ አንድ ሰው ከጣራው ላይ ቢወድቅ ለደሙ ተጠያቂ ትሆናለህ።


跟着我们:

广告


广告