Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ውዷን ተደግፋ፣ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን ወለደችህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረበዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በልጅ ወን​ድ​ምዋ ላይ ተደ​ግፋ እንደ ማለዳ ደም​ቃና አብ​ርታ የም​ት​ወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ከእ​ን​ኮይ በታች አስ​ነ​ሣ​ሁህ፤ በዚያ እና​ትህ አማ​ጠ​ችህ፥ በዚ​ያም ወላጅ እና​ትህ ወለ​ደ​ችህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 8:5
29 交叉引用  

ከእርሱ ጋር ያለው ኀይል ሰብአዊ ኀይል ነው፤ ከእኛ ጋር ሆኖ የሚረዳንና የሚዋጋልን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤” ሕዝቡም ንጉሡ በተናገረው በዚህ ቃል ተበረታታ።


ወደ አንተ እጠጋለሁ፤ ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።


እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።


ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።


እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት! ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ኑ፤ እርሱ እጅግ በተደሰተበት በሠርጉ ቀን እናቱ በራሱ ላይ የደፋችለትን ዘውድ ጭኖአል።


ከእነርሱም ጥቂት አለፍ እንዳልኩ ልቤ የምትወደውን አገኘሁት፤ እንዳያመልጠኝም አጥብቄ ያዝኩት፤ ወደ እናቴም ቤት ወሰድኩት፤ እኔ ወደተወለድኩበትም ክፍል አስገባሁት።


እንደ ነጋዴ ቅመም መልካም መዓዛ ያላት፥ በዕጣንና በከርቤ መዓዛ እየተወገደ እንደ ጢስ ዐምድ ሆና ያቺ ከበረሓ የምትመጣው ማን ናት?


ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከአማና ተራራ ጫፍ ውረጂ፤ የአንበሳና የነብር መኖሪያ ከሆኑት ከሠኒርና ከሔርሞን ተራራዎች ወርደሽ ነይ


ይህች እንደ ብርሃን የምትፈልቅ፥ እንደ ጨረቃ የምትደምቅ፥ እንደ ፀሐይ የምታበራ፥ የጦር ዓርማ ይዞ እንደሚጓዝ ሠራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ፥ እርስዋ ማን ናት?


ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክልኝ፤ በመንገድ ላይ አግኝቼ ብስምህ ማንም ሰው አይንቀኝም ነበር፤


ምንአልባት ግብጽ ትረዳኛለች ብለህ ተስፋ አድርገህ ይሆናል፤ ነገር ግን በእርስዋ መታመን በሸምበቆ የመደገፍ ያኽል መሆኑን ዕወቀው፤ ተሰንጥሮ እጅህን ከሚወጋው በቀር ሸምበቆ ለምንም አይጠቅምህም፤ በግብጽ ንጉሥ የሚተማመንም የሚገጥመው ዕድል ይህንኑ የመሰለ ነው።’ ”


እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦ “በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ! በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ!


ይልቅስ የማደርገውን አዲስ ነገር ተመልከቱ፤ እርሱም በመፈጸም ላይ ስለ ሆነ ልታዩት ትችላላችሁ፤ በበረሓ መንገድን አወጣለሁ፤ በምድረ በዳም ወንዞችን አፈልቃለሁ።


“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።


ከመልአኩም ጋር ታግሎ በረታ፤ አልቅሶም ምሕረትን ለመነ፤ ሌላ ጊዜም በቤትኤል የተገኘው እግዚአብሔር እኛን አነጋገረን።


የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።


ኢየሱስ ይወደው የነበረው፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ጐን ተቀምጦ ነበር።


ወንድሞቼ ሆይ፥ የእናንተም ሁኔታ እንደዚሁ ነው፤ እናንተ የክርስቶስ አካል ክፍል ስለ ሆናችሁ በሞት የመለየትን ያኽል ከሕግ ተለይታችኋል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍሬ እንድናፈራ ከሞት የተነሣው የክርስቶስ ወገኖች ሆናችኋል።


ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ ላይ ተቀርጾ እስኪታይ ድረስ እንደገና ስለ እናንተ በምጥ ጭንቅ ላይ እገኛለሁ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።


ሴቲቱም ወደ በረሓ ሸሽታ ሄደች፤ እዚያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን በእንክብካቤ ተይዛ የምትጠበቅበትን ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶላት ነበር።


跟着我们:

广告


广告