Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 7:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዘንባባው ዛፍ ላይ ወጥቼ ፍሬውን መልቀም እወዳለሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ዕቅፍ ይሁኑ፤ የእስትንፋስሽ መዓዛ እንደ ፖም ፍሬ ሽታ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ። ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣ የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኮይ ፍሬ ይሁኑ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ፥ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህ ቁመ​ትሽ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ይመ​ስ​ላል፥ ጡቶ​ች​ሽም የወ​ይን ዘለላ ይመ​ስ​ላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህ ቍመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የወይን ዘለላ ይመስላሉ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 7:8
10 交叉引用  

የምትቀባው ሽቱ መልካም መዓዛ አለው፤ ስምህን መጥራት ሽቱን እንደ መርጨት ነው፤ ቈነጃጅትም የሚያፈቅሩህ ስለዚህ ነው።


ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።


እኔ በፍቅሩ ተይዤ ስለ ታመምኩ ዘቢብ እየመገባችሁ አበረታቱኝ፤ በፖም ፍሬም አስደስቱኝ።


የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።


ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ ጡቶችሽም ዘለላውን ይመስላሉ።


እኔም ለእነርሱ መልካም ነገር በማድረግ ደስ ይለኛል፤ እኔ በፈቃዴ በዚህች ምድር በእውነት እመሠርታቸዋለሁ።


የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል።


ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን!


跟着我们:

广告


广告