Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህች እንደ ብርሃን የምትፈልቅ፥ እንደ ጨረቃ የምትደምቅ፥ እንደ ፀሐይ የምታበራ፥ የጦር ዓርማ ይዞ እንደሚጓዝ ሠራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ፥ እርስዋ ማን ናት?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣ እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይህች እንደ ማለዳ ብር​ሃን የም​ት​ጐ​በኝ፥ እንደ ጨረቃ የተ​ዋ​በች እንደ ፀሓ​ይም የጠ​ራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰ​ለፈ ሠራ​ዊት የም​ታ​ስ​ፈራ ማን ናት?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 6:10
24 交叉引用  

ከዝናብ በኋላ ደመና እንደሌለው ንጋት፥ ምድርንም ሣር እንድታበቅል እንደሚያደርግ፥ እንደ ንጋት የፀሐይ ብርሃን ነው።”


ሕይወትህ ከቀትር ፀሐይ ይበልጥ ይበራል፤ ጨለማው እንደ ማለዳ ብርሃን ይሆናል።


የፀሐይን ማሸብረቅ፥ የጨረቃን መድመቅ ተመልክቼ፥


እግዚአብሔር የሚገኘው ከጻድቃን ጋር ስለ ሆነ እነርሱ በፍርሃት ይሸበራሉ።


የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል።


ፍቅሬ ሆይ! እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ውብ ናቸው።


እንደ ነጋዴ ቅመም መልካም መዓዛ ያላት፥ በዕጣንና በከርቤ መዓዛ እየተወገደ እንደ ጢስ ዐምድ ሆና ያቺ ከበረሓ የምትመጣው ማን ናት?


ፍቅሬ ሆይ! እንደ ቲርጻ ከተማ የተዋብሽ ነሽ፤ እንደ ኢየሩሳሌምም እጅግ ያማርሽ ነሽ፤ የጦር ዓርማ ይዞ እንደሚጓዝ ሠራዊት የሚያስፈራ ግርማ አለሽ።


በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ።


“ይህን ብታደርጉ ብርሃናችሁ እንደ ንጋት ብርሃን ያበራል፤ ፈውሳችሁም በፍጥነት ይመጣል፤ ፈራጃችሁ በፊታችሁ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔር ክብር የኋላ ደጀን ይሆናችኋል።


ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።


ለእናንተ ስሜን ለምታከብሩ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላችኋል፤ ፈውስንም ይሰጣችኋል። ከጒረኖ እንደ ተለቀቀ ጥጃ ትቦርቃላችሁ።


ጻድቃን ግን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


እዚያ በፊታቸው መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ እንደ ብርሃን አንጸባረቀ።


እንግዲህ በወደደን በክርስቶስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ድል በመንሣት ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


በዚህ ዐይነት ዕድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መጥፎ ነገር ሳይገኝባት ቅድስት፥ እንከን የሌለባትና ውብ አድርጎ ወደራሱ ያቀርባታል።


በቀኝ እጁ ሰባት ኮከቦችን ይዞ ነበር፤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ከአፉ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ።


ከዚህ በኋላ ደመና የለበሰ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱ ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ፥ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤


ከዚህ በኋላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን የለበሰች፥ ጨረቃን ከእግርዋ በታች ያደረገች፥ ዐሥራ ሁለት ኮከቦችን እንደ አክሊል በራስዋ ላይ የደፋች፥ አንዲት ሴት ታየች።


የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላትና በጉ መብራትዋ ስለ ሆነ ከተማይቱ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም።


“እኔ ኢየሱስ ይህን ምስክርነት እንዲሰጣችሁ መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያን ልኬአለሁ፤ እኔ የዳዊት የትውልድ ሐረግና ዘር ነኝ፤ የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነኝ።”


ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


跟着我们:

广告


广告