ማሕልየ መሓልይ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ለውዴ በሩን ከፈትኩለት። ውዴ ደርሶ ተመለሰ፤ ድምፁን ለመስማት እጅግ ጓጉቼ ነበር፤ አጥብቄ ፈለግኹት፤ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም፤ ጠራሁት፤ እርሱ ግን አልመለሰልኝም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ለውዴ ከፈትሁለት፤ ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዷል፤ በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ለልጅ ወንድሜ ከፈትሁለት፥ ልጅ ወንድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም። 参见章节 |