Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ፍቅሬ ሆይ! እንዴት ውብ ነሽ! እንዴት ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ያማሩ ናቸው፤ ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ ላይ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ ዐይኖችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ርግቦች ናቸው፥ ጠጉርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ከዝ​ም​ታሽ በቀር ዐይ​ኖ​ችሽ እንደ ርግ​ቦች ናቸው፤ ጠጕ​ርሽ በገ​ለ​ዓድ ተራራ እን​ደ​ሚ​ታይ እንደ ፍየል መንጋ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፥ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 4:1
17 交叉引用  

በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው።


ፍቅሬ ሆይ! እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ውብ ናቸው።


ውዴ እንዲህ ይለኛል፥ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ፤


አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።


እባክሽ ዐይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ፤ እነርሱ እኔን ማርከው እስረኛ አድርገውኛል። ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ ላይ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።


ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈሉ የሮማን ፍሬ ፍንካች ይመስላሉ።


የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ ዞማው ጠጒርሽም የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው። ንጉሡም በሹሩባሽ ውበት ተማርኮአል።


“የይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት የገለዓድን አገርና የሊባኖስን ተራራዎች ያኽል ለእኔ የተዋበ ነው፤ ነገር ግን ማንም የማይኖርበት ባድማ አደርገዋለሁ።


ግርማ ሞገሴን በአንቺ ላይ አሳርፌ የተዋብሽ ስላደረግሁሽ እንከን ከሌለበት ቊንጅናሽ የተነሣ በሁሉ አገር ታወቅሽ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።


የሮቤልና የጋድ ነገዶች እጅግ ብዙ የከብት መንጋ ነበራቸው፤ የያዕዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ተስማሚ መሆኑን ባዩ ጊዜ፥


ስለዚህም ሙሴ የገለዓድን ምድር ለማኪር ቤተሰብ ሰጣቸው፤ እነርሱም በዚያ ኖሩ።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህና ትሑት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።


እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።


跟着我们:

广告


广告