Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነሆ፥ የሰሎሞን ሠረገላ እየመጣች ነው፤ ከእስራኤል ኀያላን መካከል የተመረጡ ሥልሳ የክብር ዘበኞች አጅበዋታል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን መካከል ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ፥ የሰ​ሎ​ሞን አልጋ ናት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ስድሳ ኀያ​ላን በዙ​ሪ​ያዋ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 3:7
12 交叉引用  

እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጽር በር የመጠበቅ ኀላፊነት ባላቸው የዘብ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፤


ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እነርሱ ባለሥልጣኖች፥ ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር።


ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።


ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።


ውዴ ሆይ! አንተም እኮ ውብ ነህ፤ እጅግም ደስ ታሰኛለህ፤ አልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ደስ የሚያሰኝ ነው።


እንደ ነጋዴ ቅመም መልካም መዓዛ ያላት፥ በዕጣንና በከርቤ መዓዛ እየተወገደ እንደ ጢስ ዐምድ ሆና ያቺ ከበረሓ የምትመጣው ማን ናት?


ሁሉም በሰይፍ አያያዝ የሠለጠኑና በጦርነትም የተፈተኑ ናቸው፤ በሌሊት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመመከት እያንዳንዱ ሰይፉን እንደ ታጠቀ ያድራል።


ንጉሥ ሰሎሞን በሠረገላው ውስጥ የሚቀመጥበት ዙፋን ከሊባኖስ እንጨት የተሠራ ነው፤


ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ የሚድኑትን ሰዎች ለማገልገል የሚላኩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት አይደሉምን?


ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።


ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው።


የወንድና የሴት አገልጋዮቻችሁን፥ ምርጥ ከብቶቻችሁንና አህዮቻችሁን ወስዶ ለራሱ መጠቀሚያ ያደርጋቸዋል።


跟着我们:

广告


广告