Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የዙፋኑ ምሰሶዎች በብር የተለበጡ ናቸው፤ የራስ ማስደገፊያው በወርቅ ያጌጠ ነው፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት በፍቅር አስውበው በጠለፉት ጌጥ የተዋበ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ምሰሶዎቹን ከብር፣ መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ፍቅር የተለበጠ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን የብር አደ​ረገ፥ መደ​ገ​ፊ​ያ​ው​ንም የወ​ርቅ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ሐም​ራዊ ግምጃ አደ​ረገ፤ ውስጡ ሰን​ፔር በሚ​ባል ዕንቍ የተ​ለ​በጠ ነው። ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ይልቅ እወ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 3:10
8 交叉引用  

አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! አስደናቂ ነገሮች ስለ አንቺ ተነግረዋል።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ስሙኝ፤ እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ የመልኬ ጥቊረት እንደ ቄዳር ድንኳን ነው፤ ውበቴ ግን እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎች ነው።


ንጉሥ ሰሎሞን በሠረገላው ውስጥ የሚቀመጥበት ዙፋን ከሊባኖስ እንጨት የተሠራ ነው፤


ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።


ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ ይህችም ከተማ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፤ የእኔንም አዲስ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


跟着我们:

广告


广告