Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፥ ልቤ የምትወደውን ፈለግኹት፤ ፈለግኹት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሌሊቱን ሙሉ በዐልጋዬ ላይ ሆኜ፣ ውዴን ተመኘሁ፤ ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሌሊት በመኝታዬ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሌሊት በም​ን​ጣፌ ላይ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ፈለ​ግ​ሁት፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሌሊት በምንጣፌ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 3:1
16 交叉引用  

አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም።


ምንም ያኽል ብትበሳጩ ኃጢአት አትሥሩ፤ በምትተኙበት ስፍራ በጸጥታ ልባችሁን መርምሩ።


ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።


ውዴ ሆይ! እስቲ ንገረኝ፤ የበጎችህን መንጋ የምታሰማራው የት ነው? በቀትርስ ጊዜ ዕረፍት ያገኙ ዘንድ እንዲመሰጉ የምታደርገው የት ነው? አንተን በመፈለግ የጓደኞችህን መንጋ በመከተል ፊትዋን እንደ ሸፈነች ሴት የምቅበዘበዘው ለምንድን ነው?


ለውዴ በሩን ከፈትኩለት። ውዴ ደርሶ ተመለሰ፤ ድምፁን ለመስማት እጅግ ጓጉቼ ነበር፤ አጥብቄ ፈለግኹት፤ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም፤ ጠራሁት፤ እርሱ ግን አልመለሰልኝም።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ እኔ ከፍቅሩ የተነሣ መታመሜን እንድትነግሩት ዐደራ እላችኋለሁ።


ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።


በሚገኝበት ጊዜ እግዚአብሔርን ፈልጉት፤ በሚቀርብበትም ጊዜ ጥሩት።


“በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ።


ማርያም ይህን በሰማች ጊዜ በፍጥነት ተነሥታ ወደ እርሱ ሄደች።


ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤


ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።


跟着我们:

广告


广告