Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የቤታችን ምሰሶ የሊባኖስ ዛፍ ነው፤ ጣራውም በጥድ እንጨት የተዋቀረ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የቤታችን ተሸካሚዎች ዝግባዎች፣ የጣራችን ማዋቀሪያዎችም ጥዶች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የቤታችን ሠረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥ የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የቤ​ታ​ችን ሰረ​ገላ የዝ​ግባ ዛፍ ነው፥ የጣ​ሪ​ያ​ች​ንም ማዋ​ቀ​ሪያ የጥድ ዛፍ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የቤታችን ሰረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥ የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 1:17
13 交叉引用  

የእያንዳንዱ ፎቅ ቁመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንጻ ከዋናው ሕንጻዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ሠረገሎች የተያያዘ ነበር።


በዚህ አኳኋን ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖሱ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ለበደው።


የቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል በጥድ እንጨትና በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ሆኖ የዘንባባና የሰንሰለት ቅርጽ ተስሎበት ነበር።


ደጋግ ሰዎች እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ።


የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ ዞማው ጠጒርሽም የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው። ንጉሡም በሹሩባሽ ውበት ተማርኮአል።


እርስዋ ቅጽር ብትሆን ኖሮ የብር ማማ እንሠራላት ነበር፤ እርስዋ የቅጽር በር ብትሆን ኖሮ ከሊባኖስ ዛፍ ሳንቃ የታነጸ መዝጊያ እንሠራላት ነበር።


ይህ ሰው “ለራሴ ትልቅ ቤት ከሰፊ ሰገነት ጋር እሠራለሁ፤ እንዲሁም ሰፋፊ መስኮቶችን አወጣለታለሁ፤ ቤቱን በሰፋፊ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስጌጠዋለሁ፤ ደማቅ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ” ይላል።


ሦስቱም ወደ ውስጥ ገባ ያሉ በዙሪያቸው ክፈፍ ያሉአቸው መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ግድግዳዎቻቸውም ከወለሉ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት የተለበዱ ነበሩ፤ የመስኮቶቹ መዝጊያዎችም በዚሁ የተሠሩ ነበሩ።


ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል።


ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው።


跟着我们:

广告


广告