Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ፍቅሬ ሆይ! እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ውብ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ ዐይኖችሽም እርግቦች ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዐይ​ኖ​ች​ሽም እንደ ርግ​ቦች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ ዓይኖችሽም እንደ ርግቦች ናቸው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 1:15
17 交叉引用  

ውዴ ሆይ! አንተም እኮ ውብ ነህ፤ እጅግም ደስ ታሰኛለህ፤ አልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ደስ የሚያሰኝ ነው።


አንቺ ከሴቶች ሁሉ ያማርሽ ውብ ሆይ! ቦታውን የማታውቂው ከሆነ የበጎቹን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።


ውዴ ሆይ! የፈርዖንን ሠረገሎች በሚስቡ ፈረሶች መካከል ያለችውን ውብ ባዝራ ትመስያለሽ፤


ውዴ እንዲህ ይለኛል፥ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ፤


በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤ የወይን ተክልም አብቦአል፤ የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤ ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ።


ፍቅሬ ሆይ! እንዴት ውብ ነሽ! እንዴት ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ያማሩ ናቸው፤ ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ ላይ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።


ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛል፤ የሽቶሽ መዓዛ ከማንኛውም ሽቶ ይበልጣል።


ፍቅሬ ሆይ! ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ ምንም እንከን የለብሽም።


ዐይኖቹ በወንዝ አጠገብ እንደሚታዩና በወተት የታጠቡ እንደሚመስሉ ርግቦች ያምራሉ።


እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።”


ይህች እንደ ብርሃን የምትፈልቅ፥ እንደ ጨረቃ የምትደምቅ፥ እንደ ፀሐይ የምታበራ፥ የጦር ዓርማ ይዞ እንደሚጓዝ ሠራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ፥ እርስዋ ማን ናት?


ፍቅሬ ሆይ! እንደ ቲርጻ ከተማ የተዋብሽ ነሽ፤ እንደ ኢየሩሳሌምም እጅግ ያማርሽ ነሽ፤ የጦር ዓርማ ይዞ እንደሚጓዝ ሠራዊት የሚያስፈራ ግርማ አለሽ።


ውዴ ሆይ! እንዴት ያማርሽ ነሽ? እንዴትስ ውብ ነሽ? ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል?


ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ ጡቶችሽም ዘለላውን ይመስላሉ።


“ስለምን መሥዋዕታችንን አይቀበልም?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እግዚአብሔር መሥዋዕታችሁን የማይቀበለው የቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁ ለሆኑት ለወጣትነት ሚስቶቻችሁ ታማኝነታችሁን ስላፈረሳችሁ ነው፤ በእናንተም መካከል እግዚአብሔር ምስክር ነበር።


跟着我们:

广告


广告