Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የጉንጮችሽ ውበት እንደ ከበረ ሉል ነው፤ አንገትሽም በዕንቊ ጌጥ የተዋበ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጕንጮችሽ በጕትቻ፣ ዐንገትሽም በዕንቍ ሐብል አጊጠዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጉንጭሽ ውበት በከበረ ሉል፥ አንገትሽም በዕንቁ ድሪ ያማረ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥ አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የጕንጭሽ ውበት በከበረ ሉል፥ አንገትሽም በዕንቍ ድሪ ያማረ ነው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 1:10
14 交叉引用  

ግመሎቹ ጠጥተው ካበቁ በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያኽል የሚመዝን የወርቅ ጒትቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያኽል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፥


እኔም ‘የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም ‘የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ’ አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጒትቻ በጆሮዋ ላይ፥ አንባሮቹንም በእጆችዋ ላይ አደረግሁላት፤


ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፥ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።


ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።


እነርሱም ለራስህ ክብርን እንደሚያቀዳጅ ዘውድ፥ ለአንገትህም ውበትን እንደሚሰጥ ሐብል ይሆኑልሃል።


እኛ ግን የብር ፈርጥ ያለው የወርቅ ጌጥ እናሠራልሻለን።


ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ የዐይኖችሽ አመለካከትና የአንገትሽ ድሪ ልቤን ማርኮታል፤


የጉንጮቹ ማማር ጣፋጭ ሽታ ያላቸው የቅመማቅመም ዕፀዋት እንደሚገኙበት የአትክልት ቦታ ነው፤ ከንፈሮቹ መዓዛው የሚጣፍጥ የከርቤ ሽቶ እንደሚያፈሱ የአሸንድዬ አበባዎች ናቸው።


እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ ማለትም የእግር አልቦውን፥ የእጅ አንባሩን፥ የጣት ቀለበቱን፥ የጆሮ ጒትቻውንና የአንገት ድሪውን ሁሉ ለኃጢአታችን ማስተስረያ ለእግዚአብሔር ቊርባን ይሆን ዘንድ ይዘን መጥተናል።”


ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።


跟着我们:

广告


广告