Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህም ከሆነ በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር ማረፍ እወዳለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይኸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተም ጋራ እንድታደስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር እንዳርፍ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ በደ​ስታ ወደ እና​ንተ መጥቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ዐርፍ ዘንድ ነው።

参见章节 复制




ሮሜ 15:32
18 交叉引用  

ቀዝቃዛ ውሃ በሙቀት ጊዜ የሚያረካውን ያኽል ታማኝ መልእክተኛም የላከውን ሰው ያረካል።


ነገር ግን “የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ሌላ ጊዜ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ” አላቸውና ከኤፌሶን በመርከብ ተሳፍሮ ሄደ።


ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።


ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜም የክርስቶስን በረከት በሙላት ይዤላችሁ እንደምመጣ ዐውቃለሁ።


እነርሱ የእኔን መንፈስና የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋል፤ ስለዚህ እንደእነዚህ ያሉትን ሰዎች ዕወቁአቸው።


ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ የእነዚህን ትዕቢተኞች ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን ኀይላቸውንም ማወቅ እፈልጋለሁ።


ከመጽናናታችንም በላይ ቲቶ ባገኘው ደስታ ይበልጥ ተደስተናል፤ የተደሰትነውም ሁላችሁም ቲቶን ስላጽናናችሁትና መንፈሱንም ስላሳረፋችሁት ነው።


ጌታ ለኦኔሲፎር ቤተሰቦች ምሕረትን ይስጥ፤ እርሱ ብዙ ጊዜ አጽናንቶኛል፤ በመታሰሬም አላፈረም።


እንግዲህ ወንድሜ ሆይ! ይህን መልካም ነገር እንድታደርግልኝ በጌታ እለምንሃለሁ፤ እባክህ ልቤን በክርስቶስ አድስልኝ።


ወንድሜ ሆይ! በአንተ ምክንያት የምእመናን ልብ ስለ ታደሰ ፍቅርህ ታላቅ ደስታንና መጽናናትን ሰጥቶኛል።


ይልቁንስ እናንተ ማለት የሚገባችሁ “ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ነው።


跟着我们:

广告


广告